ስማርት ጉዞ የዘመናዊ ባስ ቲኬቲንግ አገልግሎት ሥራ መጀመሩን አሳወቀ

ሰላምቴክ ቢዝነስ ኃ.የተ.የግ ማህበር በያዝነው የሰኔ ወር ስማርት ጉዞ የተሰኘ የሀገር አቋራጭ ባስ ትራንስፖርት የትኬት ሸያጭና አስተዳደር ቴክኖሎጂ በይፋ ሥራ ማስጀመሩን ገለጸ። ይህም ቴክኖሎጂ ለመንገደኞች የጉዞ ትኬት ለመቁረጥ የሚያባክኑትን ጊዜ እና ጉልበትም በመቆጠብ ባሉበት ቦታ ሆነው የጉዞ ትኬት መቁረጥ የሚችሉበት ቴክኖሎጂ ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ ስማርት ጉዞ ከሐበሻ ባስ ጋር የውል ስምምነት ፈጽሞ አብሮ እየሰራ ሲሆን ቴክኖሎጂውንም ከሐበሻ ባስ ሠራተኞች ጋር ለማስተዋወቅም የተለያዩ ስልጠናዎችን ሰጥቶ በማጠናቀቅ ወደ ስራ ለማስገባት እየሰራ ነው።

ከሐበሻ ባስ መድረሻዎች ማለትም ወደ ጎንደር፣ ባህር ዳር፣ ሞጣ፣ ደብረማርቆስ፣ ደብረወርቅ፣ ቢቼና፣ ደሴ፣ ኮሶበር፣ ቡሬ፣ ፍኖተሰላም፣ ደምበጫ፣ ሀዋሳ፣ አርባምንጭ፣ ወላይታ፣ ሚዛን፣ ጅማ፣ ቦንጋ፣ ጋምቤላ፣ ነቀምቴ፣ መቱ እና በደሌ ለሚደረጉ ጉዞዎች ስማርት ጉዞ የትኬት መቁረጫ አማራጮችን ያካትታል።


ተሳፋሪዎች በስማርት ጉዞ በቀላሉ ባሉበት ቦታ ሆነው የጉዞ ትኬት ለመቁረጥ እንዲያስችላቸው የተለያዩ አማራጮችን ይዞ የመጣ ሲሆን ከእነዚህም መካከል በጥሪ ማዕከል 9211 በመደወል፣በድህረ ገጽ አድራሻ www.smartguzo.com እንዲሁም በስማርት ስልክ የስማርት ጉዞ መተግበሪያን በመጠቀም ባሻቸው የባስ አይነት፣ በፈለጉት የወንበር ቁጥር እንዲሁም በመረጡት የክፍያ አማራጮች (በቀጥታ በባንኮች በመክፈል እንዲሁም በኦንላይን ) ክፍያ መፈፀም ይችላሉ።


ስማርት ጉዞ ለወደፊት ከያዛቸው ዕቅዶች ውስጥ ይህን የትራንስፖርት ትኬት ሸያጭና አስተዳደር ቴክኖሎጂ ከዘመኑ ጋር በማስኬድ የተሻለ ለማድረግ እንዲሁም ከሌሎች የልዩ ባስ ሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት ከሚሰጡ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመስራት ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል::

Categories:

Tagged:

Comments are closed

Categories

Latest Comments

No comments to show.