አጋር ፈንድ የሥራ ጅማሮ

በሰላምቴክ ቢዝነስ ኃ.የተ.የግል ማህበር ተሰርቶ ለኢትዮጵያውያን የቀረበው አጋር ፈንድ የተሰኘው በአይነቱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነው የክራውድ ፈንዲንግ ድህረ ገጽ በኢትዮጵያ መቀመጫቸውን ያደረጉ ልዩ ልዩ ተቋማት፤ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ግለሰቦች በታመነለት ምክንያት ድጋፍን በቀላሉ በኦንላይን ገንዘብ ለማሰባሰብ የሚችሉበት ድህረ ገጽ ነው።

ይህም ማንኛውም ሰው ወይም ተቋም ያለምንም ቅድመ ክፍያ የፋይናንስ አቅማቸውን ለማሳደግ እና ላጋጠማቸው የማህበራዊ ፣ የኢኮኖሚ እንዲሁም የጤና ምክንያቶች ፈጣን እና አስተማኝ የቴክኖሎጂ አማራጭ ነው።
ይህ አጋር ፈንድ የተሰኘው በኦንላይን የገንዘብ ማሰባሰብያ ፖርታል በሁለት አማራጮች የቀረበ ሲሆን በድህረ ገጽ www.agarfund.com እንዲሁም በስማርት ስልክ አጋር ፈንድ መተግበሪያ መጠቀም ያስችላል።

በተጨማሪም በአሁኑ ጊዜ የሙከራ ሂደቱን በማጠናቀቅ በአዲስ መልክ ልዩ ልዩ አዳዲስ ሃሳቦችና አሰራሮችን አካቶ በተሻለ ሁኔታ ለመጀመር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ይህም ማንኛውም ህጋዊ የገንዘብ ድጋፍን ለማሰባሰብ ለሚፈለጉ ግለሰቦችም ይሁን ድርጅቶች ሁነኛ የቴክኖሎጂ አማራጭ ሆኖ ቀርቧል፡፡

ቴክኖሎጂው ለመጠቀም ቀላልና አስተማማኝ ከመሆኑም በላይ ያለምንም ቅድመ ክፍያ አገልገሎትን ለማግኘትም እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም በታመነለት ምክንያት የገንዘብ ድጋፍና ከሀገር ውስጥም ይሁን ከውጪ ለማሰባሰብ የሚፈልጉ ኢትዩጵያውያን ወደ ድህረ ገጹ በመግባት በመመዝገብ ዘመቻን መክፈት ይችላሉ፡፡ ለማንናውም ጥያቄና አስተያየትም ድህረ ገጹ ላይ ባሉት የደንበኞች አገልግሎት  አራማጮች መጠቀም እንደሚቻልም ተገልጻል፡፡

Categories:

Tagged:

Comments are closed

Categories

Latest Comments

No comments to show.